am_1ki_text_ulb/01/38.txt

1 line
711 B
Plaintext

\v 38 ስለዚህ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን ወረዱ፤ ሰሎሞንን በንጉሥ ዳዊት በቅሎ ላይ በማስቀመጥ ወደ ግዮን አመጡት። \v 39 ካህኑ ሳዶቅ ዘይት ያለበትን ቀንድ ከድንኳን ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው። በዚያን ጊዜ መለከት ነፉ፣ ሕዝቡም፣ “ንጉሥ ሰሎሞን ለዘላለም ይኑር!” አሉ። \v 40 ሕዝቡም ሁሉ ተከትሎት ወጣ፣ ሕዝቡም እምቢልታ እየነፉ በታላቅ ደስታ ደስ አላቸው፣ ከድምፃቸው የተነሣ ምድር ተንቀጠቀጠች።