am_1ki_text_ulb/01/32.txt

1 line
661 B
Plaintext

\v 32 ንጉሥ ዳዊትም፣ “ካህኑን ሳዶቅን፣ ነቢዩን ናታንን እና የዮዳሄን ልጅ በናያስን ጥሩልኝ” አለ። እነርሱም በንጉሡ ፊት ቀረቡ። \v 33 ንጉሡም እንዲህ አላቸው፡- የጌታችሁን አገልጋዮች ከእናንተ ጋር ውሰዱ፤ ልጄን ሰሎምንንም እኔ በምቀመጥባት በቅሎ አስቀምጡትና ወደ ግዮን አውርዱት። \v 34 ካህኑ ሳዶቅና ነቡዩ ናታን ቀብተው በእስራኤል ላይ ያንግሡትና መለከት በመንፋት “ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!” በሉ።