am_1ki_text_ulb/01/24.txt

1 line
557 B
Plaintext

\v 24 ናታንም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ‘አዶንያስ ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለሃልን? \v 25 እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችን፣ የሰቡ ጥጆችንና በጎችን ሠውቷል፤ ደግሞም የንጉሡን ልጆች ሁሉ፣ የሠራዊቱን አዛዥ ኢዮአብንና ካህኑን አብያታርን ጋብዟል። ንጉሥ አዶንያስ ለዘላለም ይኑር! በማለት በፊቱ በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው፡፡