am_1ki_text_ulb/01/15.txt

1 line
637 B
Plaintext

\v 15 ስለዚህ ቤርሳቤህ ወደ ንጉሡ ክፍል ሄደች። ንጉሡ እጅግ ስለ ሸመገለ ሱነማይቱ አቢሳ ታገለግለው ነበር። \v 16 ቤርሳቤህም ራስዋን ዝቅ አድርጋ ለንጉሡ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት፡፡ \v 17 እርሷም እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ ሆይ፣ ለአገልጋይህ፣ ‘በእርግጥ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ በአምላክህ በጌታ እግዚአብሔር ስም ምለህ ነበር፡፡