Tue Jun 26 2018 10:48:00 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2018-06-26 10:48:00 +03:00
parent e85505bc61
commit 54af35bc5a
8 changed files with 14 additions and 0 deletions

1
19/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 እግዚአብሔርም ኤልያስን ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም አለው፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኮረብቶችን ሰነጣጠቀ፤ ዐለቶችንም ሰባበረ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፡፡ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም፡፡ \v 12 ከምድሪቱም ነውጥ በኋላ እሳት መጣ፤ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም፤ ከእሳቱም በኋላ የሹክሹክታ ድምፅ ተሰማ፡፡

1
19/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 ኤልያስ የሹክሹክታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጎናጸፊያ ሸፈነ፤ ወጥቶም በዋሻው መግቢያ በር አጠገብ ቆመ፤ አንድ ድምፅም ኤልያስ ሆይ፣ እዚህ ምን ታደርጋለህ? ሲል ጠየቀው፡፡ \v 14 ኤልያስም ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ፣ እኔ ለአምላኬ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔን እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ ሲል መለሰ፡፡

1
19/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 15 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ በደማስቆ ከተማ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓ ተመልሰህ ሂድ፤ እዚያም በደረስህ ጊዜ አዛሄልን ቀብተህ በሶርያ ላይ አንግሠው፤ \v 16 የናሜሲን ልጅ ኢዩንም ቀብተህ በእስራኤል ላይ አንግሠው፤ የአቤል ምሖላ ተወላጅ የሆነውን የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕንም ቀብተህ በአንተ ፈንታ ነቢይ እንዲሆን አድርገው፡፡

1
19/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 ከአዛሄል እጅ ከመገደል ተርፎ የሚያመልጠውን ማንኛውንም ሰው ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩ እጅ የሚያመልጠውንም ኤልሳዕ ይገድለዋል፡፡ \v 18 ይሁን እንጂ ለእኔ ታማኞች የሆኑ ለባዓል ያልሰገዱና ለምስሉም ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን በእስራኤል ምድር በሕይወት እንዲተርፉ አደርጋለሁ፡፡

1
19/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 19 ኤልያስም ከዚያ ከሄደ በኋላ የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ሁለት በሬዎች ጠምዶ ሲያርስ አገኘው፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ በአሥራ አንድ ጥማድ በሬዎች የሚያርሱ ደቦኞች ነበሩ፤ ኤልሳዕም በመጨረሻ አሥራ ሁለተኛውን ጥማድ ያርስ ነበር፤ ኤልያስም መጎናጸፊያውን አውልቆ በኤልሳዕ ላይ ደረበለት፡፡ \v 20 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ተቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ አባቴና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ አለው፡፡ ኤልያስም፣ እሺ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም! ሲል መለሰለት፡፡

1
19/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 21 ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ወደ ጥማድ በሬዎቹ ተመልሶ አረዳቸው፡፡ የተጠመዱበትንም ቀንበር በማንደድ ሥጋቸውን ቀቅሎ ለሰዎቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ከዚህ በኋላ ኤልያስን ተከትሎ በመሄድ ረዳቱ ሆነ፡፡

1
20/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 20 \v 1 የሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፡፡ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ያሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያ ጦርነት ገጠመ፡፡ \v 2 እርሱም ሀዳድ በከተማይቱ ወደሚገኘው ወደ እስራኤል ነጉሥ ወደ አክዓብ፣ ቤን ሀዳድ እንዲህ ይላል ብሎ መልእክተኞችን ላከ፡- \v 3 ብርህና ወርቅህ ውብ የሆኑት ሚስቶችህና ልጆችህ ምርጥ የሆኑ ሁሉ የእኔ ናቸው፡፡

View File

@ -354,7 +354,14 @@
"19-04",
"19-07",
"19-09",
"19-11",
"19-13",
"19-15",
"19-17",
"19-19",
"19-21",
"20-title",
"20-01",
"21-title",
"22-title"
]