am_1ki_text_udb/20/33.txt

1 line
1.3 KiB
Plaintext

\v 33 የቤን ሀዳዳ ባለሥልጣኖች አክዓብ ምህረት የማድረግ አሳብ ያለው መሆኑን ለማወቅ በመሞከር ላይ ነበሩ፡፡ አክአብ ወንድም ብሎ በመናገሩ ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ በመሆኑም እንዲህ ብለው መለሱለት “አው እንደወንድምህ ነው” አክአብ እንዲህ አለ “ሂዱና ወደኔ አምጡት፡፡” ስለዚህ ሄደው ቤን ሀዳድን ወደ እርሱ አመጡት ቤን ሐዳድ ወደ ሥፍራው በደረሰ ጊዜ ሠረገላው ላይ እንዲወጣ እና ከእርሱ ጋር እንዲቀመጥ አክዓብ ነገረው፡፡ \v 34 ያኔ ቤን ሀዳድ እንዲህ አለው “የአባቴ ጦር ከአባትህ የወሰዳቸውን ከተሞች እመልስልሀለሁ፡፡ በዋና ከተማዬ ባደማስቆም በዋና ከተማህ በሠማርያ አባቴ እንዳደረገው ለነጋዲዎችህ የንግድ ሥፍራዎች እንድትመሠርትም ፈቅድልሀለሁ” አክዓብ እንዲህ በማለት መለሰለት “ያን ስለምታደርግ አልገልህም” ስለዚህ አክዓብ ከቤን ሀዳድ ጋር አንድ ስምምነት አደረገና እንዲሄድ ፈቀደለት፡፡