am_1ki_text_udb/20/09.txt

1 line
835 B
Plaintext

\v 9 ስለዚህ አክዓብ ለቤን ሀዳድ መልእክተኞች እንዲሀ አላቸው “መጀመሪያ የጠየቀኝን ነገሮች ለመስጠት የምስማማ መሆኔን ለንጉሥ ንገሩት ባለሥልጣኖቹ ከቤተ መንግሥቴ እና ከባለሥልጣናቶቼ ቤት የፈለጉትን ነገር እንዲወስዱ ግን አልፈቀድም” ይህንኑ መልእክተኞቹ ለንጉሥ ቤን ሀዳድ ነገሩት እና ኬቤን ሀዳድ ሌላ መልእክት ይዘው ተመለሱ፡፡ \v 10 በዚያ መልእክቱ እንዲህ አለ “ወታደሮቼ እያንዳንዳቸው እፍኝ አመድ ለመዝገን እስኪያጡ ድረስ ከተማህን ሙሉ በሙሉ እናወድማታለን ያን ባላደርግ አማልክት መትተው ይግደሉኝ”