am_1ki_text_udb/18/43.txt

1 line
869 B
Plaintext

\v 43 ከዚያም አገልጋዩን እንዲህ አለው “ሂድና የዝናብ ደመና መኖር አለመኖሩን ለማየት ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት” አገልጋዩ እንደታዘዘው ሄደ በምልክት ተመለሰና “ምንም አላየሁም አለ” ይህ ለስድስት ጊዜ ተከናወነ \v 44 አገልጋዩ ለሰባተና ጊዜ ከሄደ በኋላ ግን ተመለሶ መጣና እንዲህ አለ “ከባሕሩ በላይ በጣም ትንሽ ደመና አየሁ፡፡ እጄን ሥዘረጋ የደመናው መጠን መዳፌን ያክላል” ኤልያስ ድምፁን ከፍ አደረገና “ወደ ንጉሥ አክአብ ሂድና ሠረገላውን አዘጋጅቶ ቶሎ ወደ ቤቱ እንዲሄድ ንገረው ያን ካላደረገ ዝናቡ አያስኬደውም አለው፡፡”