am_1ki_text_udb/13/26.txt

1 line
888 B
Plaintext

\v 26 ነቢዩን ከይሁዳ ወደቤቱ ያመጣው ሽማግሌ ስለነገሩ በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ “ይህ ሰው እግዚአብሔር እንዲያደርግ ያዘዘውን ያልታዘዘ ነው ለዚህ ነው እግዚአብሔር አንበሳ እንዲያጠቃውና እንዲገድለው የፈቀደው እግዚአብሔር ይሆናል ያለውም ይህ ነው፡፡” \v 27 ከዚያም ልጆቹን “አህያም ላይ ኮርቻ አድረጉ አለ” ያዘዛቸውን አደረጉ \v 28 በአህያው እየጋለበ ሄደና የነቢዩን አስከሬን መንገዱ ላይ አገኘው የሟቹ አህያ እና አንበሳውም እስከዚያን ጊዜ እሬሣው አጠገብ ቆመው ነበር፡፡ አንበሳው ከነብዩ አስከሬን ምንም አልበላም አህያውንም አልነካውም፡፡