am_1ki_text_udb/13/11.txt

1 line
688 B
Plaintext

\v 11 ያኔ ቤቴል ውስጥ የሚኖር አንድ ዕድሜው የገፋ ሰው ነበር ሰውየው ነቢይም ነበር፡፡ ልጆቹ መጥተው ከይሁዳ የመጣው ነቢይ ያን ዕለት እዚያ ያደረገውን እና ለንጉሡ ያለውን ነገሩት፡፡ \v 12 አባታቸው እንዲህ አለ “በየትኛው መንገድ ነው የሄደው” ከይሁዳ የመጣው ነቢይ ከቤቴል ወጥቶ የሄደበትን መንገድ ልጆቹ አሳዩት፡፡ \v 13 እርሱም ለልጆቹ እንዲህ አላቸው “አህያዬ ላይ ኮርቻ አድርጉልኝ፡፡” አደረጉለትና አህያው ላይ ወጣ፡፡