am_1ki_text_udb/12/28.txt

1 line
1.1 KiB
Plaintext

\v 28 ስለዚህ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማከረና የመከሩትን አደረገ ከወርቅ የተሠሩ የሁለት ጥጃዎች ሐውልት እንዲሠሩ ለሠራተኞቹ ነገረ፡፡ ከዚያም ለሕዝቡ እንዲህ አለ “ለማምለክ ወደ ኢየሩሳሌም ስትሄዱ ብዙ ጊዜ ሆኗችኋል፡፡ እናንተ የእሥራኤል ሕዝቦች ተመልከቱ ቀደምት አባቶቻችንን ከግብጽ ያወጧቸው እነዚህ ሀውልቶች ናቸው ስለዚህ እነዚህን ልታመልኩ ትችላላችሁ” እዚሁ \v 29 ከሀውልቶቹ አንዱን ቤቴል ከተማ ውስጥ በስተ ደቡብ እና በስተሰሜን ዳን ከተማ ውስጥ እንዲያስቀምጡ ለሠራተኞቹ ነገራቸው፡፡ \v 30 በመሆኑም ኢዮርብዓም ያደረገው ነገር ሕዝቡን ኃጢአት እንዲሠሩ አደረጋቸው፡፡ አንዳንዶቹ ወደ ቤቴል እየሄዱ የጥጃውን ሀውልት አመለኩ፣ የቀሩት ደግሞ ሌላውን የጥጃ ሀውልት ለማምለክ ወደ ዳን ሄዱ፡፡