am_1ki_text_udb/12/12.txt

1 line
716 B
Plaintext

\v 12 ከሦስት ቀን በኋላ ኢዮርብዓምና መሪዎቹ ሁሉ ቀደም ብሎ በቀጠራቸው መሠረት እንደገና ወደሮብዓም መጡ፡፡ \v 13 ንጉሡ የአረጋውያኑን ምክር በመተው እሥራኤላውያኑን መሪዎች በከባድ ቃላት ተናገራቸው፡፡ \v 14 ወጣቶቹ ሰዎች የመከሩትን ነገራቸው እንዲሁ በማለት “አባቴ የከባድ ሥራዎች ሸክም አሸክሟችሁ ነበር እኔ ግን ይበልጥ የከበዱ ሸክሞች አሸክማችኋለሁ፡፡ እርሱ በአለንጋ እንደገረፋችሁ እኔ ግን በጊንጥ እንደምገርፋችሁ ማለት ነው፡፡”