am_1ki_text_udb/08/22.txt

3 lines
963 B
Plaintext

\v 22 ከዚያም ሰለሞን በዚያ ሥፍራ በተሰበሰበው የእሥራኤል ሕዝብ ፊት በነበረው መሠዊያ ፊት ለፊት ቆሞ እጆቹን ወደ ሰማይ
\v 23 በመዘርጋትም እንዲህ እያለ ጸለየ “እኛ የእሥራኤል ሕዝቦች የምናመልከህ እግዚአብሔር ሆይ በሰማይ ወይም በዚህ በምድር አንተን የሚመስል አምላክ የለም፡፡ በታማኝነት እንደምትወደን ቃል ቃል ገብተሀል፡፡ አንተ እንድናደርግ የፈለከውን በቅንነት ለምናደርገው ለእኛ ያደረከው ያንኑ ነው፡፡
\v 24 በሚገባ ላገለገለህ ለአባቴ ለዳዊት የገባህለትን ነገሮች አደረክ እነዚህን ለእርሱ እንደምታደርግለት በእውነት ቃል ገባህ እና የተናገርከውን በኃይልህ ስታደርግ ዛሬ አየን፡፡