\v 6 ከዚያም ካሕናቱ የተቀደሰውን ታቦት ቤተመቅደሱ ውስጥ ወደ አለው ቅድስተ ቅዱሳት አመጡት እና ክንፉም በሆኑት ፍጡራን ሀውልት ክንፍ ሥር አኖሩት፡፡ \v 7 የነዚያ ሀውልቶች ክንፎች በታቦቱ እና የእርሱ መሸከሚያ በሆኑት እንጨቶች ላይ ተዘርግተዋል፡፡ \v 8 እንጨቶቹ በጣም ረጃጅም ናቸው፡፡ በመሆኑም የእንጨቶቹ ጫፍ ወደ ቅድስቱ ቅዱሳኑ መግቢያ በር ላይ ለቀመሰው ሊታዩ ይችሉ ነበር ከቤተመቅደሱ ውጭ በቆሙ ሰዎች ግን አይታዩም፡፡ እነዚያ እንጨቶች አሁንም አሉ፡፡