am_1jn_text_ulb/04/11.txt

1 line
677 B
Plaintext

\v 11 ወዳጆች ሆይ!እግዚአብሔር ይህን ያህል ከወደደን፣እኛም እርስ በርሳችን መዋደድ ይገባናል። \v 12 ማንም እግዚአብሔርን አላየውም። እርስ በርሳችን ብንዋደድ፣ እግዚአብሔር በኛ ይኖራል፣ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል፡፡ \v 13 መንፈሱን ሰጥቶናልና፣ በዚህም እኛ በእርሱ እንደምንኖር፣ እርሱም በኛ እንደሚኖር እናውቃለን። \v 14 እኛም አይተናል፣እግዚአብሔር ልጁን የዓለም አዳኝ አድርጐ እንደላከውም እንመሰክራለን፡፡