\v 11 ከመጀመሪያው የሰማችኋት መልእክት፣ይህ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ የሚለው ነው። \v 12 ክፉ እንደሆነውና ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም። የገደለው ለምንድን ነው ? ምክንያቱ የራሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ ጽድቅ ስለነበረ ነው፡፡