am_1jn_text_ulb/03/01.txt

1 line
784 B
Plaintext

\c 3 \v 1 የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን!በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም። \v 2 የተወደዳችሁ፣አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፤ምክንያቱም ትክክለኛ ማንንነቱን እናየዋለን። \v 3 በእርሱም ላይ ይህ ጽኑ እምነት ያለው ሁሉ፣ እርሱ ንፁህ እንደሆነ ራሱን ያነፃል፡፡