am_1jn_text_udb/03/16.txt

1 line
1.0 KiB
Plaintext

\v 16 ወገኖቻችንን በእውነት የምንወድበትን መንገድ አሁን የምናውቀው ክርስቶስ በራሱ ነጻ ፈቃድ ለእኛ ኃጢአት መሞቱን በማስታወስ ነው፡፡ ስለዚህ በተመሳሳ መንገድ፣ እኛም ለአማኝ ወገኖቻችን ለእነርሱ እስከ መሞት ድረስ ማንኛውንም ነገር ማድረግ አለብን፡፡ \v 17 ብዙዎቻችን በዚህ ዓለም ለመኖር የሚያስፈልጉን ነገሮች አሉን፡፡ ከአማኝ ወገኖቻችን መሃል ለመኖር የሚያስፈልጋቸው እንደሌላቸው አውቀን ለእነርሱ ለማቅረብ ባንፈቅድ እንደምንናገረው እግዚአብሔርን እንደማንወድ ግልጽ ነው፡፡ \v 18 ለምወዳችሁ ለእናንተ ይህን እናገራለሁ፣ እርስ በእርሳችን እንደምንዋደድ በአፍ ብቻ አንናገር፤ እርስ በእርሳችን በመረዳዳት አንዳችን ሌላችንን እንውደድ!