am_1jn_text_udb/02/12.txt

1 line
1.1 KiB
Plaintext

\v 12 ልጆቼ ለምወዳችሁ ለእናንተ ይህን እጽፍላችኋለሁ፡፡ ክርስቶስ ለእናንተ ካደረገው የተነሳ እግዚአብሔር ኃጢአታችሁን ይቅር ብሏል፡፡ \v 13 ለሽማጊሌዎች እጽፍላችኋለሁ፤እናንተ ዘለዓለማዊ የሆነውን ክርስቶስን አውቃችሁታል፡፡ ለእናንተ ለወጣቶች ደግሞ እጽፍላችኋለሁ፤እናንተ ክፉ የሆነውን ሰይጣንን አሸንፋችሁታል፡፡ ለእናንተ ልጆች ለሆናችሁ እጽፍላችኋለሁ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አብን አውቃችኋል፡፡ \v 14 ደግሜ እላለሁ፡ ለእናንተ ለሽማግሌዎች እጽፍላችኋለሁ ምክንያቱም ዘለዓለማዊ የሆነውን ክርስቶስን ወደ ማወቅ መጥታችኋል፡፡ ደግሞም ለወጣቶች እጽፋለሁ፤ ምክንያቱም እናንተ ብርቱዎችና የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የምትጠብቁ ናችሁ፣ እናም ክፉ የሆነውን ሰይጣንን ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡