am_1jn_text_udb/02/01.txt

2 lines
1.1 KiB
Plaintext

\c 2 \v 1 ልጆቼ ለእኔ ተወዳጆች የሆናችሁ ሆይ፣ ከኃጢአት ትርቁ ዘንድ ይህን እጽፍላችኋለሁ፡፡ ነገር ግን ከእናንተ ማናችሁም ኃጢአት እንደሰራችሁ ብታምኑ፣ ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታ እንዲያደርግልን ከአባቱ ዘንድ ምህረትን እንደሚለምንልን አስታውሱ፡፡ \v 2 ክርስቶስ በፍቃዱ ህይወቱን ለእኛ ሰውቷል፣ ስለዚህም በውጤቱ እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ብሏል፡፡ አዎን፣ እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ማለት ይችላል፣ ነገር ግን የእኛን ብቻ አይደለም! እርሱ በሁሉም ስፍራ ያሉ ሰዎችን ኃጢአት ይቅር ሊል ይችላል!
\v 3 እንደምናውቅ እንዴት እርግጠኛ መሆን እንደምንችል እነግራችኋለሁ፡፡ እርሱ እንድናደርገው ያዘዘንን ብንታዘዝ፣ ይህ ከእርሱ ጋር ህብረት እንዳለን ያሳያል፡፡