am_1jn_text_udb/05/16.txt

1 line
1012 B
Plaintext

\v 16 ምናልባት ከአማኝ መሃል አንዱ ከእግዚአብሔር የማይለየውን ኃጢአት ሲሰራ ታዩ ይሆናል፣ እናም ኃጢአት ሲሰራ ስታዩ፣ እግዚአብሔር ለዚያ ሰው ህይወት እንዲሰጠው እርሱን መለመን ይኖርባችኋል - ይህም ያ ሰው ከእግዚአብሔር የሚለየው ኃጢአት ያልሰራ ከሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ሊለይ በሚችል መንገድ ኃጢአት የሚሰሩ አንዳንድ አሰዎች አሉ፡፡ በዚህ አይነት መንገድ ኃጠአት የሚሰሩትን ሰዎች እግዚአብሔር እንዲረዳቸው መጸለይ አለባችሁ እያልኩ አይደለም፡፡ \v 17 እግዚአብሔር ላይ በማመጽ የሚሰራ ኃጢአት አለ፣ ነገር ግን ማናቸውም የሚሰሩ መጥፎ ነገሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር ለዘለዓለም ሊለዩ አይችሉም፡፡