am_1jn_text_udb/05/06.txt

1 line
1005 B
Plaintext

\v 6 ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስቡ፡፡ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ምድር የመጣ ነው፡፡ እግዚአብሔር በእውነት ኢየሱስን እንደላከው ያሳየው ዮሐንስ ኢየሱስን በውሃ ውስጥ ሲያጠምቅ ነው፣ ነገር ግን፣ ደግሞም ሲሞት የኢየሱስ ደም ከሰውነቱ ሲፈስ ነው፡፡ እናም የእግዚአብሔር መንፈስ በዕውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ዘንድ እንደመጣ ይመሰክራል፡፡ \v 7 እነዚህ ሶስት ነገሮች እንደ ሶስት ምስክሮች ናቸው፡ \v 8 የእግዚአብሔር መንፈስ፣ ዮሐንስ ኢየሱስን ሲያጠምቅ ውሃው፣ እና በመስቀል ላይ ሲሞት የፈሰሰው የኢየሱስ ደም፡፡ እነዚህ ሶስቱ ሁሉም ተመሳሳይ ነገር ይነግሩናል፣ ይህም ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ መምጣቱ ነው፡፡