am_1jn_text_udb/05/01.txt

1 line
765 B
Plaintext

\c 5 \v 1 ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን የሚያምኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለዱ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፡፡ አማኝ ወገኖቻችን ሆይ፣ አብን የሚወድ ሁሉ ወልድን ይወዳል፡፡ \v 2 የእግዚአብሔርን ልጆች መውደዳችንን እርግጠኛ መሆን የምንችልበት መንገድ፣ እግዚአብሔርን መውደድና እርሱ አድርጉ ብሎ ያዘዘንን ማድረግ ነው፡፡ \v 3 ይህን የምናገርበት ምክንያት እግዚአብሔርን መውደድ ማለት እርሱ ያዘዘንን ማድረግ ስለሆነ ነው፡፡ እርሱ ያዘዘውን ማድረግም አስቸጋሪ አይደለም፡፡