am_1jn_text_udb/01/05.txt

1 line
1.1 KiB
Plaintext

\v 5 ከእግዚአብሔር የሰማነውና ለእናንተ የምንነግራችሁ መልእክት ይህ ነው፡ እርሱ በፍጹም ኃጢአት አላደረገም፡፡ እርሱ ጨለማ እንደሌለበት ፍጹም አንጸባራቂ ብርሃን ነው፡፡ \v 6 ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት አለን የምንል ከሆነ፣ ነገር ግን ህይወታችንን ባልጸዳ ሁኔታ ከመራን፣ ይህ በክፉ ጨለማ ውስጥ እንደ መኖር ነው፡፡ እንዲህ ካደረግን እየዋሸን ነው፡፡ ህይወታችንን በእግዚአብሔር እውነተኛ መልዕክት እየመራን አይደለም ማለት ነው፡፡ \v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር በሁሉም መንገድ ንጹህ ሆኖ እንደሚኖር በንጽህና መኖር በእግዚአብሔር ብርሃን እንደ መኖር ነው፡፡ ይህን ካደረግን፣ እርስ በእርሳችን ህብረት ይኖረናል፤ ኢየሱስ ለእኛ ሰለሞተም እግዚአብሔር ይቅር ይለናል፤ ይቀበለናልም፡፡