am_1jn_text_udb/01/01.txt

1 line
760 B
Plaintext

\c 1 \v 1 እኔ፣ዮሐንስ ምንም ነገር መኖር ከመጀመሩ አስቀድሞ ስለነበረው እጽፍላችኋለሁ! እኛ ሐዋርያት እርሱ ሲያስተምር ሰምተነዋል! አይተነዋል! እኛ ራሳችን እርሱን አይነተናል ነክተነዋልም! ስለ ዘለዓለማዊ ህይወት ያለውን መልዕክት ያስተማረን እርሱ ነው፡፡ \v 2 (እርሱ ወደዚህ ወደ ምድር ስለመጣና እኛ ስላየነው፣ ለእናንተ በግልጽ የምንሰብከው ከዘለዓለም የነበረውንና ያየነውን ነው፡፡ እርሱ አስቀድሞ በሰማይ ከአባቱ ጋር ነበር፣ ነገር ግን በእኛ መሃል ለመኖር መጣ፡፡)