am_1co_text_ulb/06/01.txt

1 line
658 B
Plaintext

ከእናንተ አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ክርክር ቢኖረው፤ በቅዱሳን ፊት ስለጉዳዩ ከመነጋገር ይልቅ በማያምን ዳኛ ፊት ለመቆም ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ይደፍራልን? ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን?በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፤ ትናንሽ ጉዳዮችን መፍታት አትችሉምን? በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁምን? እንግዲህ በዚህ ዓለም ሕይወት ጉዳዮች ላይ የበለጠ ለመፍረድ እንዴት አንችልበት?