am_1co_text_ulb/05/03.txt

1 line
656 B
Plaintext

እኔ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ከእናንተ ጋር አለሁ፤ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ ባደረገው ሰው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ። እናንተ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በምትሰበሰቡበት ጊዜ መንፈሴም ከጌታችን ኢየሱስ ኃይል ጋር እዚያው በመካከላችሁ አለ፤ይህ ሰው በጌታ በኢየሱስ ቀን ይድን ዘንድ፤ ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።