ጥበበኛ ሰው የት አለ? ዐዋቂስ የት አለ? የዚህ ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚህ ዓለም ጥበብን ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን? ዓለም በጥበብዋ እግዚአብሔርን ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል።