በክርስቶስ ኢየሱስ ስለተሰጣችሁ ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ሁልጊዜ ስለእናንተ አምላኬን አመሰግናለሁ። በነገር ሁሉ፤በንግግርና በዕውቀት ሁሉ ባለጸጋ እንድትሆኑ አድርጎአችኋልና። ስለክርስቶስ የተሰጠው ምስክርነት በመካከላችሁ እውነት ሆኖ እንደጸና ሁሉ ባለጸጎች አድርጎአችኋል።