ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በስተቀር ማናችሁንም ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ስለዚህ ማናችሁም በእኔ ስም እንደተጠመቃችሁ ለመናገር አትችሉም። የእስጢፋኖስን ቤተ ሰብ ደግሞ አጥምቄአለሁ፤ ከዚህ ውጪ ሌላ ማንን አጥምቄ እንደሆነ አላውቅም።