am_1co_text_ulb/13/11.txt

1 line
812 B
Plaintext

\v 11 ልጅ በነበርሁበት ጊዜ፣እንደ ልጅ እናገር ነበር፣እንደ ልጅም አስብ ነበር፣የመረዳት ችሎታዬም እንደ ልጅ ነበር። ጎልማሳ ስሆን ግን የልጅነት ነገሮችን አስወገድሁ። \v 12 አሁን በጨለማ ውስጥ ያለን ምስል በመስታዋት እንደሚያይ እንመለከታለን፣የዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን ዕውቀትን በከፊል አውቃለሁ፣የዚያን ጊዜ ግን ልክ እኔ ሙሉ በሙሉ እንደምታወቀው ሙሉ በሙሉ አውቃለሁ። \v 13 ነገር ግን እምነት፣ ተስፋ፣ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ግን ጸንተው ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጠው ፍቅር ነው።