እያንዳንዱ ሰው እንደጠራው ዓለማና ጌታ በሰጠው ሕይወት ብቻ ይመላለስ። ይህ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የእኔ ድንጋጌ ነው። ማንም ተገርዞ ወደ እምነት ተጠርቶአልን? ወደ አለመገረዝ መመለስ የለበትም። እንዲሁም ማንም ሳይገርዝ ወደ እምነት ተጠርቶአልን? መገረዝ የለበትም። የእግአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ ነው እንጂ መገረዝ ወይም አለመገረዝ የሚያመጠው ችግር የለም።