\c 9 \v 1 እኔ ነፃ አይደለሁም? እኔ ሐዋርያስ አይደለሁም? ጌታችን ኢየሱስን አላየሁትም? እናንተስ በጌታ የሥዬ ፍሬዎች አይደላችሁም? \v 2 ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ቢያንስ ለእናንተ ሐዋርያ ነኝ። በጌታ ሐዋርያ ለመሆኔ እናንተ ማረጋገጫ ናችሁና።