am_1co_text_ulb/01/07.txt

1 line
468 B
Plaintext
Raw Normal View History

ስለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጉጉት ስትጠባበቁ አንድም መንፈሳዊ ስጦታ አይጎድልባችሁም። ይህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል። ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።