am_1ch_text_ulb/29/01.txt

1 line
845 B
Plaintext

\c 29 \v 1 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፤ ''እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና ልምድም የሌለው ነውው። ይህ ታላቅ ሕንጻ የሚሠራውን ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔ አምላክ በምሆን፣ ጅራው ከባድ ነው። \v 2 እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናስ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ጅራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሞሆነው መረግድ፣ ኬልቄዶን፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ።