am_1ch_text_ulb/26/26.txt

1 line
617 B
Plaintext

\v 26 ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተሰቡ ኅላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያት ቅድሳት ኅላፊዎች ነበሩ። \v 27 በጦርነቱ ከተገኘውም ምርኮ ከፊሉን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ማደሻ እንዲሆን ቀደሱት። \v 28 ባለ ራእይ ሳሙኤል፣ የቂስ ልጅ ሳኦል፣ የኔር ልጅ አቤኔር፣ ቅድሳት ሰሎሚናትና ቤተ ዘመዶቹ ይጠብቁ ነበር።