am_1ch_text_ulb/25/06.txt

1 line
724 B
Plaintext

\v 6 እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በጽናጽል፣ በመሰንቆ በበገና አገልግሎት በአባቶቻቸው አመራር ሥር ነበሩ። አሳፍ፣ ኤዶታምና ኤማን ደግሞ በንጉሥ የበላይ አመራር ሥር ነበሩ። \v 7 እነዚህም ከቤተዘመዶቻቸው ጋር በመሆን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር በሚቀርበው ዜማ የሠለጠኑ የተካኑ ነበሩ፤ ቁጥራቸውም ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ። \v 8 የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ።