am_1ch_text_ulb/12/16.txt

1 line
575 B
Plaintext

\v 16 \v 17 16ሌሎች ከብንያምና ከይሁዳም ወገን የሆኑ ሰዎች ዳዊት ወደሚገኝበት ምሽግ መጡ።17ዳዊትም እነዚህን ሰዎች ሊቀበል ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤የመጣችሁት ልትረዱኝና በሰላም ከሆነ፤ከእኔ ጋር እንድትሰለፉ ልቀበላችሁ ዝግጁ ነኝ፤ነገር ግን እጄ ከበደል ንጹሕ ሆኖ ሳለ፤ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ፤የአባቶቻችን አምላክ ይመልከተው፤ይፍረድውም።