am_1ch_text_udb/05/20.txt

1 line
904 B
Plaintext

20 የእነዚህ ሦስት ነገድ ሰዎች በጦርነቱ ጊዜ እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ በእርሱ ተማምነዋልና እርሱ ረዳቸው፡፡ አጋራውያንንና የጦር ተባባሪዎቻቸውን ሁሉ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ 21 የአጋራውያንንም እንስሶች ሁሉ ማረኩ፤ ሃምሳ ሺህ ግመሎች፣ ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ በጐች፣ ሁለት ሺህ አህዮች ወሰዱ፡፡ አንድ መቶ ሺህ ሰዎችንም ማርከው ነበር፡፡ 22 እግዚአብሔር የሮቤልን፣ የጋድንና የምናሴን ነገድ ስለ ረዳ ብዙ አጋራውያን ተገድለው ነበር፡፡ በባቢሎናውያን ሰራዊት ተማርከው ወደ ባቢሎን እስከ ተወሰዱ ጊዜ ድረስ እነዚህ ሦስት ነገዶች በዚያ አካባቢ ኖሩ፡፡