am_1ch_text_udb/09/33.txt

1 line
634 B
Plaintext

33 ከሌዋውያን አንዳንዶቹ ቤተ መቅደሱ ውስጥ በዘማሪነት ያገለግሉ ነበር፡፡ የእነዚህ ወገኖች አለቆች የሚኖሩት ቤተ መቅደሱ ውስጥ ባሉት ክፍሎች ነበር፡፡ ቀንና ሌሊት በዝማሬ የማገልገል ኃላፊነት ስለ ነበረባቸው ሌላ ምንም ሥራ አልነበረባቸውም 34 እነዚህ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣ የነገዱ ሰዎች ስም በሰፈረበት መዝገብ ስማቸው ተጽፎአል፤ ሁሉም የሚኖሩት በኢየሩሳሌም ነበር፡፡