am_1ch_text_udb/15/01.txt

1 line
552 B
Plaintext

\c 15 1 ዳዊት በኢየሩሳሌም ቤት እንዲሠራለት አዘዘ፤ ለታቦቱ ማረፊያ ድንኳን እንዲተከልም አዘዘ፡፡ 2 ዳዊትም፣ ‹‹ታቦቱን እንዲሸከሙና ለዘላለም እንዲያገለግሉት ያህዌ የመረጠው እነርሱን ስለሆነ ሌዋውያን ብቻ ታቦቱን ይሸከሙ›› አለ፡፡ ዳዊትም የያህዌን ታቦት እርሱ ወዳዘጋጀላት ቦታ ለማምጣት የእስራኤልን ሕዝብ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ፡፡