17 በእያንዳንዱ ቀን የምሥራቁ በር በስድስት የሰሜኑን በር በአራት፣ የደቡብ በር በአራት ወደ ግምጃ ቤቱ የሚያስገባው በር በሁለት ሌዋውያን ይጠበቅ ነበር፡፡ 18 የምዕራቡ በር ላይ አደባባዩን የሚጠብቁ ሁለት ሰዎች ከአደባባዩ ውጪ ያለውን መንገድ የሚጠብቁ አራት ሰዎች፣ ተመድበው ነበር፡፡ 19 እነዚህ የቤተ መቅደሱን በሮች የሚጠብቁ የቀዓትና የሜራሪ ዘሮች ናቸው፡፡