am_1ch_text_udb/16/04.txt

1 line
834 B
Plaintext

4 በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እንዲያገለግሉና የእስራኤል አምላክ ያህዌን የሚያመልኩ፣ የሚወድሱትን፣ የሚያመሰግኑትን ሕዝብ እንዲመሩ ዳዊት አንዳንድ ሌዋውያንን ሾመ፡፡ 5 ጸናጽል የሚጸነጽለው አሳፍ ዋና መሪ ሲሆን፣ ዘካርያስ ደግሞ የእርሱ ረዳት ነበር፡፡ አሳፍን የሚረዱ ሌሎች ሌዋውያን ይዒኤል፣ ሰሚራሞት፣ ይሔኤል፣ መቲትያ፣ ኤልያብ፣ በናያስ፣ ዖቤድኤዶምና ይዒኤል ነበሩ፤ እነርሱም በመሰንቆና በበገና ይዘምሩ ነበር፡፡ 6 እንዲሁም ካህናቱ በናያስና የሕዚኤል ዘወትር በታቦቱ ፊት መለኮት እንዲነፉ ተመደቡ፡፡