4 ሳኦልም መሣሪያዎቹን ይይዝለት የነበረውን ሰው፣ ‹‹እነዚህ አረማውያን የበለጠ እንዳያሰቃዩኝና መሣቂያ እንዳያደርጉኝ ሰይፍህን አውጣና ግደለኝ፡፡›› አለው፡፡ መሣሪያውን ይይዝለት የነበረው ሰው ግን በጣም ፈርቶ ስለ ነበር፣ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ፡፡