|
20 እነዚህ የኤፍሬም ዘሮች ናቸው፡፡ ከኤፍሬም ወንዶች ልጆች አንዱ ሼቱላ ሲሆን እርሱም ባሬድን ወለደ፤
|
|
ባሬድ ታሐትን ወለደ፤
|
|
ታሐት አልዓዳን ወለደ
|
|
የአልዓዳ ልጅም እንዲሁ ታሐት ተብሏል፡፡
|
|
21 ታሐት ዛባድን ወለደ፤
|
|
ዛባድ ሹተላን ወለደ፤
|
|
ኤድርና አልዓድ የተባሉት ከብቶች ለመስረቅ ወደ ጋድ ሄደው በነበረ ጊዜ በአገሩ ሰዎች ተገደሉ፡፡ 22 አባታቸው ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ ዘመዶቹም መጥተው አጽናኑት፡፡
|