# አጋንንት ያደሩበት አጋንንት ያደሩበት ሰው የሚያደርገውንና የሚያስበውን የሚቆጣጠሩ አጋንንት ወይም ክፉ መናፍሳት ውስጥ ይኖራሉ። * አጋንንት ያደሩበት ሰው ብዙ ጊዜ ራሱን ወይም ሌሎችን ይጎዳል፤ እንደዚያ የሚያስደርጉት ውስጡ ያሉት አጋንንት ናቸው። * ከውስጣቸው አጋንንቱ እንዲወጡ በማዘዝ ኢየሱስ አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎችን ነጻ አውጥቶአል። ብዙ ጊዜ ይህ፣ “አጋንንትን ማስወጣት” የሚባለው ነው።