# መለየት መለየት አንድን ነገር ወይም ሰው እግዚአብሔርን እንዲያገለግል መመደብ ማለት ነው። በዚህ መልኩ የተለየ ሰው ወይም እቃ ለእግዚአብሔር እንደ ተቀደሰና እንደ ተለየ ይቆጠራል። * የዚህ ቃል ትርጕም፣ “መቀደስ” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ሥርዓት ባለው መልኩ አንድን ሰው ለእግዚአብሔር አገልግሎት መለየት የሚለውንም ይጨምራል። * ለእግዚአብሔር የተለየ ነገሮች የመሥዋዕት እንስሳትን፣ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያንና መገናኛው ድንኳንን ወይም ቤተ መቅደሱንም ይጨምራሉ። * ለእግዚአብሔር የተለዩ ሰዎች ካህናትን፣ የእስራኤል ሕዝብንና ያደጉ ወንድ ልጆችን ይጨምራል። * እንደነጹና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ሰዎችን ወይም ነገሮችን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ዝግጁ ማድረግን ከሆነ፣ “መለየት” የሚለው ቃል አንዳንዴ፣ “ማንጻት” ከተሰኘው ጋር ተመሳሳይ ትርጕም ይኖረዋል።