# ቤተ ክርስቲያን በአዲስ ኪዳን መሠረት ቤተ ክርስቲያን የሚባለው ለመጸለይና የእግዚአብሔር ቃል ሲሰበክ ለመስማት ዘወትር የሚሰበሰቡ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች ስብስብ ነው። “ቤተ ክርስቲያን” ብዙውን ጊዜ፣ ክርስቲያኖችን ሁሉ ያመለክታል። * ቃል በቃል የሚያመለክተው ለተለየ ዓላማ በአንድነት የሚሰበሰቡ፣ “ተጠርተው የወጡ” ሰዎችን ጉባኤ ወይም ስብስብን ነው። * ቃሉ በክርስቶስ አካል ውስጥ በየትኛውም ቦታ ያሉ አማኞችን ሁሉ ለማመልከት ጥቅም ላይ ሲውል ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ለመለየት አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች በእንግሊዝኛው ቃል መጀመሪያ ላይ ያለውን ፊደል በትልቁ ይጽፋሉ። * ብዙውን ጊዜ በአንድ ከተማ ውስጥያሉ አማኞች የሚሰበሰቡት በግለ ሰብ ቤት ውስጥ ነበር። እነዚህ ቤተ ክርስቲያኖች የነበሩበት ከተማ ስም ይሰጣቸው ነበር። ለምሳሌ፣ “የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን” እንደሚለው።