# ክርስቲያን ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከሄደ ጥቂት ጊዜ በኋላ ስዎች “ክርስቲያን” የሚለውን ስም አወጡ፤ ክርስቲያን የክርቶስ ተከታይ ማለት ነው። * የኢየሱስ ተከታዮች ለመጀመሪያ ጊዜ፣ “ክርስቲያኖች” የተባሉት በአንጾኪያ ከተማ ነበር። * ክርስቲያን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የሚያምንና ከኃጢአት እንደሚያድነው በእርሱ የሚተማመን ሰው ነው። * በዘመናችን በእውነት የኢየሱስ ተከታይ ባይሆን እንኳ በክርስቲያን ሃይማኖት ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ክርስቲያን ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ክርስቲያን” የሚለው እንዲህ ዓይነቱን አይደለም። * መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ክርስቲያን” ሲል ሁሌም የሚያመለክተው በእውነት በኢየሱስ የሚያምን ሰውን በመሆኑ፣ ክርስቲያን፣ “አማኝ” በመባልም ይታወቃል።