# ነቀፋ የሌለበት “ነቀፋ የሌለበት” የሚለው ቃል በቃል፣ “ነውር፣ እንከን” የሌለበት ማለት ነው። በፍጹም ልቡ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ ሰውን የሚያመለክት ቢሆንም፣ ያ ሰው ምንም ኃጢአት የለበትም ማለት አይደለም። * አብርሃምና ኖኅ በእግዚአብሔር ፊት ነቀፋ የሌለባቸው ተብለዋል። * “ ነቀፋ የሌለበት” ተብሎ የሚታወቅ ሰው እግዚአብሔርኝ በሚያስከብር መንገድ ይኖራል። * አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንደሚያመለክተው ነቀፋ የሌለበት ሰው፣ “እግዚአብሔርብ የሚፈራና ከክፋትም የራቀ” ነው።